Wednesday 3 February 2016

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ መሪነቱን አጠናክሯል

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ መሪነቱን አጠናክሯል
በ8ኛው ሳምንት ከአዲስ አበባ ውጪ በተደረገ ብቸኛ ጨዋታም አዳማ ከተማ በሜዳው ከሲዳማ ቡና ጋር በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ባደረገው ጨዋታ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።
በጨዋታው ሲዳማ ቡና በ7ኛው በኤሪክ ሙራንዳ ባስቆጠራት ጎል ጨዋታውን መምራት ችሎ የነበረ ቢሆንም፥ አዳማ ከተማ ከእረፍት መልስ በ56ኛው ደቂቃ ባገኙት ፍጹም ቅጣት ምት በተስፋዬ ታፈሰ አማካት የአቻነቷን ጎል አስቆጥረዋል።
አዳማ ከተማ እስካሁን ባደረጋቸው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በሁለት ጨዋታዎች አቻ ከመውጣቱ በቀር ሁሉንም ማሸነፍ ችሏል።
በዚህም አዳማ ከተማ መሪነቱን መልሶ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ሊረከብ ችሏል።
ዛሬ በአዲስ አበባ በተደረገ ሌላ የ8ኛው ሳምንት መርሃ ግብር ጭዋታ መከላከያ ድሬዳዋ ከተማን በአዲስ አበባ ስታድየም አስተናግዶ ጭዋታውን መከላከያ ባዬ ገዛኽኝ እና ሙላለም ጥላሁን ባስቆጠሯቸው ችች 2ለ0 አሸንፏል።
ከ1 ወር መቋረጥ በኋላ ዳግም የተጀመረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ትናንት እና ከትናንት በስቲያ የተለያዩ ጭዋታዎችን አስተናግዷል።
 
ትናንት በአዲስ አበባ ስታዲይም ወላይታ ድቻን ያስተናገደው ቅዱስ ጊዮርጊስ በአዳነ ግርማ ሁለት ጎሎች እና በብራያን ኡሞኒ ጎል 3ለ0 በሆ ውጤት ማሸነፉ ይታወሳል።   
አዳነ በ49ኛው ደቂቃ ላይ የተገኘችውን ፍፁም ቅጣት ምት ወደ ግብ ሲቀይር፥ በ66ኛው ደቂቃ ላይም ሌላ አስደናቂ ግብ አክሏል።
ሶስተኛዋን ግብ ብራያን ኡሞኒ አስቆጥሮ ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ 3ለ0 አሸናፊነት የተጠናቀቀው።
ትናንት በተደረገ ሌላ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ከዳሽን ቢራ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የተጫወቱ ሲሆን፥ ኢትዮጵያ ቡና  ኤልያስ ማሞ እና ዊሊያም ያቡን ባስቆጠሯቸው ግቦች 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ዳሽን ቢራን መርታት ችሏል።
እንዲሁም ደደቢት እና አርባምንጭ ከተማ  1ለ1 በሆነ አቻ ውጤትም ተለያይተዋል።
ሰኞ እለት በተደረጉ ጨዋታዎች ኤሌክትሪክ  ሀዋሳ ከተማን 2ለ1 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ፥ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀዲያ ሆሳዕናን 1ለ0 በሆነ ውጤት መርታት ችሏል።
አዳማ ከተማ ከሲዳማ ቡና ጋር ነጥብ መጋራቱን ተከትሎ በ20 ነጥብ እና 7 ጎል ፕሪሚየር ሊጉን በአንደኝነት እየመራ ይገኛል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአዳማ ከተማ በአንድ ነጥብ ዝቅ በማለት በ19 ነጥብ 8 ጎል ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ሲዳማ ቡናም በዛሬው ጨዋታ ነጥብ ተጋርቶ መውጣቱን ተከትሎ በ13 ነጥብ ስተኝነቱን ደረጃ ከደደቢት ተረክቧል።
እንዲሁም ደደቢት በ12 ነጥብ እና በ8 ጎል አራተኛ፣ ኢትዮጵያ ቡና በ11 ነጥብ እና በ8 ንጹህ ጎል አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧዋል።

No comments:

Post a Comment